ደብረ መዉዒ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፔርኒስ - ሮተርዳም
የልጆች እና ታዳጊ ወጣቶች ክፍል በቤተ ክርሰቲያናችን ሰንበት ትምህርት ቤት ኮሚቴ ስር ሆኖ የሚያገለግል ነው።
በዚሁም መሰረት ልጆችን በሶሰት የእድሜ ክልለ ከፍሎ መሰረታዊ የቤተ ክርስቲያናችንን ትምህረት እና የአማረኛ ቛዋንቛን እያስተማረ ይገኛል። የልጆችን እና ታዳጊ ወጣቶችን የእድሜ ክልል እና የክፍል ስያሜ ከዚህ በታች ይገኛል።
1. 'ፍሬ ሃያማኖት' ክፍል (ከ4 - 7 ዓመት)
2. 'ዓምደ አይማኖት' ክፍል (ከ 8 - 13 ዓመት)
3. 'ፈለገ ህይዎት' ክፍል (ከ 13 ዓመት በላይ)
በዚህ የልጆች እና ታዳጊ ወጣቶች ክፍል ውስጥ እስተማሪዎች እና ረዳት አስተማሪዎች ተመድበው የሚያገለግሉ ሲሆን ያስማሪዎችን የማስተማር መርሃ ግብር ሰንጠረዥ በየስዎስት ወሩ እየተዘጋጀ ለሁሉም የክፍሉ አገልጋዮች የልጆች ክፍል ባዘጋጀው የቫይበር ግሩፕ በኩል እየተላክ ይደረሳቸዋል።
የማስተማርያ መርሃ ግብሩ ሰንጠረዥ በተጨማሪ በዚህ ድረ ገጽ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ በዚህ ገጽ በቀኝ በኩል ወይንም ከታች ያለውን
“የማስተማርያ መርሃ ግብር ሰንጠረዥ” የሚለውን መጠቆሚያ በመጫን ማግኘት ይቻላል።