ወጣቶቸ ክፍል >>>>>>>>>>>>>

የቴክኖሎጂ ውጤቶች ና የሉላዊነት ጫና በልጆች አስተዳደግ                                                                                      በላቸው ጨከነ ተስፋ (ዶ/ር)
መግቢያ

  1. “ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው። ” (መዝ፻፳፮፥፫) ከእግዚአብሔር የተሰጡንን በረከት በሚገባው ተንከባክቦ፣ አስተምሮ እና ጠብቆ ማሳደግ የወላጆች ትልቅ ሥራ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ “እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ። ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው። በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድም ስትሄድ ስትተኛም ስትነሳም አጫውቷቸው። እርሷንም እንዲሰጣቸው እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር እንደ ሰማይ ዘመን በምድር ላይ ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ በቤትህ መቃኖችና በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።” (ዘዳ 11፥18) እንዳለ ልጆችን ጠብቆ እና ተንከባክቦ ማሳደግ የወላጆች ትልቁ ድርሻ ነው።

    ዛሬ በተለይ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ወላጆች ለሚኖሩበት ሀገር ባህል እና ሕግ እንግዳ መሆን፣ ከልጆች ጋር የመግባቢያ ቋንቋ ችግር፣ ከቤተ ዘመድ መራቅ፣ የሥራ ጫና እና የጊዜ እጥረት፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጫና እና ዕለት ዕለት ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅርባቸው እንደልብ ስለማያገኙ የልጆችን አስተዳደግ የበለጠ ውስብስብ አድርጎታል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዘመኑን ዋጅቶ ልጆችን በሃይማኖትና በግብረ ገብ ትምህርት ለማሳደግ ከወላጆች ብዙ ይጠበቃል። በዚህ አጭር ጽሑፍ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በልጆች አስተዳደግ ላይ የፈጠሩትን ችግሮች እና የመፍቴሔ ሐሳቦች ለውላጆች ግንዛቤ ከመፍጠረ አንጻር ቀረበዋል።

    የዘመኑን የልጆች አስተዳደግ ውስብስብና አስቸጋሪ ካደረጉት ነገሮች አንዱ የመረጃ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ በቴሌቪዥን እና በኢንተርኔት የሚተላለፉ መልክቶች ናቸው። ቴክኖሎጂ የራቀውን በማቅረብ የተወሳሰበውን በማቅለል ሕይወትን የተሻለች ማድረጉ አሌ የማይባል ቢሆንም የጎንዮሽ ውጤቱም ደግሞ በተለይ ለልጆች የዚያኑ ያህል የከፋ ነው። በአግባቡ እስካልተጠቀምንበት ድረስ። ክፉና ደጉን በአግባቡ ባለየው በልጆች አዕምሮ ላይ የሚያሳርፈው ተጽዕኖ ደግሞ የከፋ ነው። በአዳጊነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን ነፍስ ካወቁ በኋላ ከትምህርታቸው የሚያዘናጋቸው፣ ከእንቅልፍ፣ ከማኅበራዊ መስተጋብር ያራራቀቸው፣ ቁምነገር እንዳይሠሩ የሚያዘናጋቸው አየሆነ ነው። የተክኖሎጂ ውጤቶች ብለን የምንመድባቸው የቪዲዮ ጌም መጫወት፣ ፊልሞች ማየት፣ የቴሌቪዥን መረሐ ግብሮች፣ ኢንተርኔት በተለይም የፌስ ቡክ ቻት፣ ዘፈን ማድመጥ፣ የተለያዩ ጨዋታዎች መመልከት የመሳሰሉት ናቸው።

Ream more ......
Share by: