የተለያዩ_Test

እንኳን ለአምላካችን ለመድሃኒ ዓለም የጥቅምት ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።



“ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው። ” (መዝ፻፳፮፥፫) ከእግዚአብሔር የተሰጡንን በረከት በሚገባው ተንከባክቦ፣ አስተምሮ እና ጠብቆ ማሳደግ የወላጆች ትልቅ ሥራ ነው::




ወደ ፊት የሚከበሩ በዓላት ዝርዝር

የቴክኖሎጂ ውጤቶች ና የሉላዊነት ጫና በልጆች አስተዳደግ   

መግቢያ

“ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው። ” (መዝ፻፳፮፥፫) ከእግዚአብሔር የተሰጡንን በረከት በሚገባው ተንከባክቦ፣ አስተምሮ እና ጠብቆ ማሳደግ የወላጆች ትልቅ ሥራ ነው። ቅዱስ መጽሐፍ “እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ። ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው። በቤትህም ስትቀመጥ በመንገድም ስትሄድ ስትተኛም ስትነሳም አጫውቷቸው። እርሷንም እንዲሰጣቸው እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር እንደ ሰማይ ዘመን በምድር ላይ ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ በቤትህ መቃኖችና በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው።” (ዘዳ 11፥18) እንዳለ ልጆችን ጠብቆ እና ተንከባክቦ ማሳደግ የወላጆች ትልቁ ድርሻ ነው።

ዛሬ በተለይ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ወላጆች ለሚኖሩበት ሀገር ባህል እና ሕግ እንግዳ መሆን፣ ከልጆች ጋር የመግባቢያ ቋንቋ ችግር፣ ከቤተ ዘመድ መራቅ፣ የሥራ ጫና እና የጊዜ እጥረት፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጫና እና ዕለት ዕለት ቅድስት ቤተክርስቲያን በቅርባቸው እንደልብ ስለማያገኙ የልጆችን አስተዳደግ የበለጠ ውስብስብ አድርጎታል። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ዘመኑን ዋጅቶ ልጆችን በሃይማኖትና በግብረ ገብ ትምህርት ለማሳደግ ከወላጆች ብዙ ይጠበቃል። በዚህ አጭር ጽሑፍ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በልጆች አስተዳደግ ላይ የፈጠሩትን ችግሮች እና የመፍቴሔ ሐሳቦች ለውላጆች ግንዛቤ ከመፍጠረ አንጻር ቀረበዋል።

Lees meer

የቤተ ክርስቲያን አገልግሎቶች

Meer informatie

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናት በኔዘርላንድ

የሰበካ መንፈሳዊ ኮሚቴ እና የተለያዩ ኮሚቶዎች የሪፖሮቶች

Meer informatie
Share by: