በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

 


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአምስተርዳም ተከፈተ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን በሆላንድ ሃገር በአምስተርዳም ከተማ ሰኞ መጋቢት ፳፱ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም ከአምስተርዳምና አካባቢው እንደዚሁም ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ምዕመናን በተገኙበት በቅዳሴና በታላቅ ድምቀት በአባታችን በብፁዕ አቡነ እንጦስ ተመርቆ ተከፈተ::

ብፁዕ አባታችንም ቤተ ክርስቲያኑን "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአምስተርዳም" ብለው ሰይመውታል:: እንደዚሁም አባታችንን አባ ገብረ ፃዲቅን "መላከ ብስራት" ብለው በመሰየም ለደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ አድርገውም ሰይመዋቸዋል::

በዚሁ የምርቃ ስነ ስርዓት ላይ ብፁዕ አባታችን ለምዕመኑ ቃል ቡራኬ ካስተላለፉ በኋላ ከፊታችን እሁድ ከሆሳዕና በዓል ጀምሮ ዘወትር እሁድ የቅዳሴ ስርዓት እንደሚከናወን ለምዕምኑ አብስረዋል፥፥

የቤተ ክርስቲያኑ ኣድራሻ፥
Handweg 117, Amstelveen 

የቅዳሴ ስርዓት ዘወትር እሁድ ፥ ከጥዋቱ 8:30

ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑት


የመጋቢት መድሃኒ ዓለምን ንግስ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ


የኢ/ኦ ተዋሕዶ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በኔዘርላንድ ፤ የጌታችንና መድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ የሆነውን የመጋቢት መድሃኒ ዓለምን ክብረ በዓል እሁድ መጋቢት ፳፰ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. (April 6, 2014) በፔርኒስ - ሮተርዳም በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ዋለ።
ብጹዕ አባታችን አቡነ እንጦስ የሰሜንና ሰ/ምዕራብ አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ በመካከላችን ተገኝተው ህዝበ ክርስቲያኑን ባርከዋል።
የበዓሉን አከባበር በቪዴዎች ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑት። 

 


ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻየሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡
መሲህ ቢመጣእንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለውያምኑ ነበር፡፡
ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡
ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትልእንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ


ገብር ኄር (የዐቢይ ጾም 6 ሳምንት)
ይህ ሳምንት የዐብይ ጾም ስድስተኛው ሳምንት ሲሆን እንደሌሎቹ ሰንበታትና ሳምንታት ሁሉ ይህም ሳምንት የራሱ የሆነ መጠሪያ አለው:: ገብር ኄር ይባላል:: ትርጓሜውም በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ ማለት ነው:: ነቢዩ ዳዊት “እስመ አንተ ትፈድዮ ለኵሉ በከመ ምግባሩ/አንተ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህና/ መዝ 61፡12 እንዳለ ጌታ ዳግም ሲመጣ ለሁላችንም እንደ ሥራችን ዋጋችንን እንደሚከፍለን የምናስብበት ሳምንት ነው:: አገልጋዮች ለአገልግሎቱ ባለቤት ሳይሆኑ ባለአደራ መሆናቸው የሚዘከርበት፣ ለታማኝ አገልጋዮች ማበረታቻ የሚሰጥበት፣ ሐኬተኛ አገልጋዮች ለንስሐ የሚጋበዙበት ወን ነው፡፡ በዕለቱ የሚዘመረው መዝሙር ቅዱስ ያሬድ እንደ ደረሰው፤ ‹‹መኑ ውእቱ ገብር ኄር፡ ታማኝ አገልጋይ ማ ነው›› የሚል ነው፡፡ ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ
ደብረ ዘይት (የዐቢይ ጾም 5 ሳምንት)
ደብረ ዘይት ማለት ቃሉ “ደብር” ሲል ተራራ ሲሆን “ዘይት” ሲል የወይራ ዛፍን ያመለከታል። ባጠቃላይ ደብረ ዘይት የወይራ ዛፍ (የዘይት ዛፍ) የበዛበት ተራራ ማለት ነው። ቦታው የሚገኘው በቅድስት አገር ኢየሩሳሌም ከጎለጎታ (ቀራንዮ) ተራራ በስተምስራቅ በግምት ፪ ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ታላቅ ተራራ ነው። በሁለቱ ተራሮች መካከል ጌቴሴማኒ የሚባለው ለምለም ስፍራ ይኸውም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የመቃብር ስፍራ ይገኛል። ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ


መፃጉዕ (የዐቢይ ጾም 4ኛ ሳምንት)

ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፥ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የምትባል አንዲት መጠመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላለሻ ነበረባት።
በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞችና ዕውሮች አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሕዝብ ይተኙ ነበር። ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡምኩራብ (የዐቢይ ጾም 3ኛ ሳምንት)
የዐብይ ጾም ሦስተኛው ሳምንት ስያሜ ‹‹ምኩራብ›› ይባላል፡፡ መድኃኒታችን በምኩራበ አይሁድ ተገኝቶ ለታሰሩት ነጻነትን፣ ለሞቱት ሕይወትን፣ ለድሆች ወንጌልን፣ ለተጠቁት ነጻነጽ፣ በፍርድ ላሉጽ ሁል ዓመተ ምህረትን ስለማስተማሩ፤ ትምህርቱን የሰሙትም በትምህርቱ ስመደነቃቸው ይነገራል የዘመራል፡፡ ስያሜው የቅዱስ ያሬድ ሲሆን መድኃኒታችን በምኩራብ የሰራቸውን ነገሮች እያስታወሰ፣ እየጠቀሰ ስለዘመረው ይህን ስያሜ አግቷል፡፡ ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ


ቅድስት (የዐቢይ ጾም 2ኛ ሳምንት)
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጾም፤ ዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ቅድስት ተብሎ የሚጠራበት ምክንያት ከዚሁ ሰንበት ዋዜማ ጀምሮ የሚዘመረው ጾመ ድጓ ቀለሙ ‹‹ዛቲ ዕለት ቅድስት ይዕቲ፤ ይህች ቀን የተቀደሰች ናት›› ‹‹ሰንበትየ ቅድስትየ እንተ አዕረፍኩ፤ ያረፍኩባት ቅድስት ሰንበት ናት›› ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ 


ዘወረደ (የዐቢይ ጾም የመጀመሪያ ሳምንት)
በአብ ስም አምነን አብን ወላዲ ብለን፤ በወልድ ስም አምነን ወልድን ተወላዲ ብለን፤ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምነን መንፈስ ቅዱስን ሰራጺ ብለን፤ ምንም ለአጠይቆ አካላት ሦስት ብንል በባሕርይ በህልውና አንድ አምላክ ብለን አምነን የአምላክን ቸርነት፤ የወላዲተ አምላክን አማላጅነት አጋዥ በማድረግ ከዛሬ ጀምሮ በዐቢይ ጾም ስምንት ሳምንታት የሚነገረውን ቃለ እግዚአብሔር (በቤተክርስቲያናችን የሚዘመረውን መዝሙር፤ የሚነበበውን ምንባብ፤ የሚቀደሰው ቅዳሴ) ከዚህ እንደሚከተለው መጻፍና መማማር እንጀምራለን፡፡ ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ 


ዓቢይ ጾም

እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ለመጾም አደረሳችሁ!!!

   ስምንቱ ሳምንታት

  1. ዘወረደ
  2. ቅድስት
  3. ምኲራብ
  4. መጻጕዕ
  5. ደብረዘይት
  6. ገብር ኄር
  7. ኒቆዲሞስ
  8. ሆሣዕና

ጌታችን መድኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተጠመቀ በኋላ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ወደ ገዳመ ቆሮንቶስ ሄደ። አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ጾመ። ከዛም ፈታኝ ዲያብሎስ ቀርቦ በስስት፣ በትእቢትና በፍቅረ ነዋይ ፈተነው። ጌታችንም ፈተናዎቹን በጥበበ አምላክነቱ ድል በማድረግ ድልን ለአዳምና ለእኛ ለልጆቹ ሰጠን (ማቴ. 4፡ 1 - 11)። ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ 


በኔዘርላንድ ደብረመዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን በሚገነባው ደጀሰላም፣ የህፃናት ትምህርት ቤት፣ ሚስጢረ ቤ/ክርስቲያን የሚፈፀምበት እና ቤ\ክርስቲያኑ በመጥበቡ የተነሣ የሚደርስብንን ስጋት ለመቀነስ ታሰቦ የልማት ኮሚቴ ተቋቁሞ ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል። ሙሉውን እዚህ ላይ በመጫን ያንብቡ 

 

 

 

home
church services
biblical studies
kids
memebership


links
contact us

songs
photos
preachings
download
The EOTC in The Netherlands, Debre Mewie St. Gebriel Church 2004