በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

   

ውድ የጌታችንና መድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶሰ ቤተሰቦች

የዘንድሮው የጌታችንና መድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ የሆነው
የጥቅምት መድሃኒ ዓለም ክብረ በዓል ከቅዳሜ ጥቅምት ፳፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም (8 November 2014) ከምሽቱ ፪ ሰዓት ጀምሮ በመንፈሳዊ መርሃ ግብርና በሌሊት ማህሌት ጸሎት በማድረስ ሲከበር አድሮ አሁድ ጥቅምት ፴ ቀን ፳፻፯ዓ.ም. (9 November 2014) ከጥዋቱ ፩ ሰዓት ጀምሮ በኪዳን ጸሎትና በቅዳሴ እንደዚሁም ታቦታትን በማንገስ በታላቅ ድምቀት ተከቦሮ ውሏል ።

የበዓሉን አከባበር ቪዲዮ ቅንብር ከዚህ በታች ይመልከቱ።

   
   

 

   
 


 
 

 

 
 

 

 


ዘመነ ጽጌ

«ድንግል ሆይ ርጉም በሆነ ሄሮድስ ዘመን ከልጅሽ ጋር ከሀገር ሀገር ስትሸሺ ከአንቺ ጋር መሰደዱን አሳስቢ ፤
ድንግል ሆይ ከዓይንሸ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት የወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ፤ ድንግል ሆይ ረሐቡንና ጥሙን፣ ችግሩንና ሐዘኑን፣ ከእርሱ ጋር የደረሰብሽንም ጭንቅ ሁሉ አሳስቢ›› ቅዳሴ ማርያምጽጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ዘመነ ጽጌ ማለት የአበባ ዘመን ማለት ነው፡፡በሀገራችን መስከረም 25 ቀን ዘመነ ክረምት አልፎ መስከረም 26 ቀን ዘመነ ጽጌ ይጀምራል፡፡ 
ዘመኑ አበቦች የሚያብቡበትና ሜዳዎችንና ተራሮችን የሚያስጌጡበት ዘመን ነው፡፡
 ፍሬ የተባለ ጌታን ያስገኘች እመቤታችን በአበባ ትመሰላለችና ዘመኑ የጌታንና 
የእመቤታችንን  ነገር በአበባና በፍሬ ለመመሰል የተመቸ ነው፡፡
ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከመስከረም 26 ቀን ጀምሮ እስከ ኅዳር 6 ቀን ድረስ የጌታን እና የእመቤታችን ስደት ታስባለች፡፡

ተጨማሪ ለማንበብ ይህንን ይጫኑ »


 

 

home
church services
biblical studies
kids
memebership

 

links
contact us
songs
photos
preachings
download