በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ውድ የጌታችንና መድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶሰ ቤተሰቦች

የዘንድሮው የጌታችንና መድኃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስ ጥንተ ስቅለቱ መታሰቢያ የሆነው 
የጥቅምት መድኃኒ ዓለም ክብረ በዓል በዋዜማው አርብ ጥቅምት ፳፮  ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. (6 November 2015) ከምሽቱ ፬ ሰዓት ጀምሮ በመንፈሳዊ መርሃ ግብርና በሌሊት ማህሌት ጸሎት በማድረስ ሲከበር አድሮ በእለቱ ከቅዳሜ ጥቅምት ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.. (7 November 2014) ከጥዋቱ ፪ ሰዓት ጀምሮ በኪዳን ጸሎትና በቅዳሴ እንደዚሁም ታቦታትን በማንገስ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል ። 

በዘንደሮው ክብረ በዓለ ላይ ወንድማችን ሊቀ ምዘምራን ይልማ ኃይሉ ሌሊት ከካሀናት አባቶችና ዲያቆናት ወንድሞች ጋር በማህሌት መዝሙር እና ጠዋት ከቅዳሴ በኋላ ከደብሩ መዘምራን ጋር በመዝሙር በማግለገል ክብረ በዓሉ በታላቅ ድምቀት ተከብሮ ውሏል፥፥

የበዓሉን አከባበር ቪዲዮ ቅንብር ከዚህ በታች ይመልከቱ።


ካህናት አባቶችና ዲያቆናት ወንድሞች እንደዚሁም ምዕመናን የማህሌት መዝሙር
ሲያቀረቡ # 1

 


ካህናት አባቶችና ዲያቆናት ወንድሞች እንደዚሁም ምዕመናን የማህሌት መዝሙር
ሲያቀረቡ # 2

 


መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ - ሙሴ ያያት በደብረ ሲና


መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ - ማነው እርሱ


መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ - ወደ በርሃን ተመላለሱ

 


መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ - ሰላም እለኪየአምላካችን የመድኃኒ ዓለም የጥቅምት ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል አከባበር

  


የደብሩ ዘማሪያን የወረብ መዝሙር ሲያቀርቡ

 


መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ - እኔስ ወደ እግዚአብሔር መሄድ ይሻለኛል


አባ ገብር ሚካኤል ከምዕመንጋራ በህብርት ሲዘምሩ

 


መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ - ገና እንዘምራለን

  


ዘመነ ጽጌ
መስከረም 27 ቀን 2008 ዓ.ም.

በሀገራችን በኢትዮጵያ የዘመን ስሌት አዲሱን ዓመት በወርኃ መስከረም አንድ ብለን መቁጠር እንደጀመርን ከምናስተውላቸው ዓበይት ክስተቶች መካከል የውኃውን መጉደል፣ የሰማዩን መጥራት እንዳለ ሆኖ ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው የምድር በአበቦች ማጌጥ ነው፡፡
ዝርዝር ንባብ...


እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ፤

"...እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ..."
ማቴዎስ ፲፮፣ ፳፬
በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ:: የ፳፻፯ ዓ.ም የመስቀል በዓል አከባበር ላይ ያቀረበው ትምህርት፤

 
የ2008 ዓ.ም ባሕረ ሐሳብ፤ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ፤ በምሥራቀ ፀሓይ ቀበና መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያንየመዝሙረ ዳዊት አራት ዋና ዋና ጥቅሞች - ስብከት በዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ ፤ ፔርኒስ - ሮተርዳም የገዳማት ቀን ሃምሌ ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ።ም (August 2, 2015)


የሊቀ መልዐኩ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በዓል አምስተርዳም በሚገኘው ደብረ ብስራት ቅዱስ ገብረዔል ቤተ ክርስቲያን በእለቱ እሁድ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም
ከሆላንድ፣ ከቤልጄም፣ ከፈረንሳይ እንድዚሁም ከጀርመን ሃገራት የመጡ የኢትዮጵያ የኤርትራ እና የሶሪያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያናት ካህናት አባቶች ዲያቆናትና ምዕመና በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።
የበዓሉን አከባበር ከዚህ በታች ባሉት ቪዲዮች ይመልከቱ:-


ለተጨማሪ ቪዲዮች ይህንን ይጫኑ


የሊቀ መልዐኩ የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ንግስ በዓል ፔርኒስ-ሮተርዳም በሚገኘው ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በእለቱ እሁድ ሐምሌ ፲፱ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያናት ካህናት አባቶች ዲያቆናትና ምዕመና በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ።

የበዓሉን አከባበር ከዚህ በታች ባሉት ቪዲዮች ይመልከቱ:-

 

ለተጨማሪ ቪዲዮች ይህንን ይጫኑ


ግንቦት ፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ማሳሰቢያ ለምእመናን በሙሉ:-

ባሕታዊ አባ ገ/ጊዮርጊስ የተባሉ በሆላንድ ሃገር በተለያዩ ከተሞች የስብከትና ሀብተ ፈውስ አገልግሎት እንደሚሰጡ በመግለጽ ምእመናን በጉባዔው እንዲሳተፉ የሚጋብዝ ጥሪ እየተሠራጨ ይገኛል ።

እኝህ ሰው የመጡት በሆላንድ የኢ/ኦ/ተ ደብረ መዊዕ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የሰበካው መንፍሳዊ  ኮሚቴም ሆነ በአምስተርዳም፣ በሮተርዳም፣ በአይንድ ሆቨን እና በአምስፎርት ከተሞች በቤተ ክርስቲያናችን ስር የሚገኙት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ተወካዮች የማያውቁት ስለሆነ ምእመኑ ጠንቅቆ እንዲገነዘብ ፅህፈት ቤቱ ያሳውቃል።

ይህንን በሚመልክት ተቀማጭነቱ በጀርመን ሃገር የሆነው የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን የምእራብ፣ የምስራቅና የድቡብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጽ/ቤት፥ በፌስ ቡካቸው ላይ ያወጡትን መልእክት እዚህ ላይ በመጫን ይመልከቱ።

 

home
church services
biblical studies
kids
memebership


 

 

links
contact us
songs
photos
preachings
download